የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አመራሮች እና ሰራተኞች በቅርቡ ተጠናቆ በተመረቀዉ
የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ ዉይይት አካሄዱ፡፡
የኤጀንሲዉ አመራሮች እና ሰራተኞች ‹‹እምርታ እና ማንሰራራት!›› በሚል መሪ ሀሳብ መጋቢት 24/2003 ዓ.ም ተጀምሮ ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም የተመረቀዉን የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ የተዘጋጀዉን ሰነድ መሰረት በማድረግ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ዉይይት በ5/01/2018 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡ የህዳሴ ግድብ ያለ ምንም የዉጭ የፋይናንስ ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት አቅም የተገነባ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት እና የመቻል ምልክት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በዉይይቱ ግድቡ ሲገነባ ገጥመዉት በነበሩ ፈተናዎች፣በግድቡ ፋይዳ፣የህዳሴ ግድብን በመገንባት ሂደት በተወሰደ ትምህርት እና መሰል ጉዳዮች የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር ተደርጓል፡፡