የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሰ የ2015 ዓ.ም የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በደብረታቦር ከተማ እያካሄደ ነው።=======
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የዋናው መስሪያ ቤት አመራሮቾና የማኔጅመንት አባላት፣ የመንገድ ጥገና ጽ/ቤቶች ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት፣ የፕሮጀክቶች ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት የሚሳተፋበት የ2015 ዓ.ም የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከሚያዝያ 17 – 18/2015 ዓ.ም ሁለት ቀን የሚቆይ ስብሰባ በደብረታቦር ከተማ ዛሬ ጀምሯል።
በአፈጻጸም ግምገማው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት በሪሁን እና ሌሎች የቢሮው ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል ።
በእቅድ አፈጻም ግምገማው ትኩረት ተሰጥቶ ውይይት ይደረግባቸዋል ተብለው የሚጠበቁት፦ በአፈጻጸም የተገኙ ስኬቶች፣ የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎች ተለይተው ከተገመገሙ በኋላ በቀሪው የበጀት ዓመቱ የስራ ጊዜ የኤጀንሲን ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ የጠበቃል።
አቅዶ መፈጸም መገለጫ በህላችን ነው !!
ጥራት ያለው መንገድ ተደራሽ ማድረግ ተልዕኳችን !!
ለተጨማሪ መረጃ
