የዋናዉ መ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የዋናዉ መ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ዉይይት አካሄዱ፡፡

በዕቅድ አፈፃፀም ዉይይቱ ላይ እንደተገለፀዉ ኤጀንሲዉ ባለፉት 9 ወራት 16.7 ኪ.ሜ መንገድ በመገንባት የ9 ወሩን ዕቅድ24.97% ፣የዓመቱን ዕቅድ ደግሞ 17.96% ፈፅሟል፡፡በመንገድ ጥገና ዘርፍ በመደበኛ እና ወቅታዊ የጥገና ዓይነቶች 2,412.04 ኪሜ የነባር መንገዶች ጥገና ሥራ በማከናወን የ9 ወሩን ዕቅድ72.26% ፣የዓመቱን ዕቅድ ደግሞ 52.89% አከናዉኗል፡፡

በ9ወሩ የተመዘገበዉ አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆኑ የተገመገመ ሲሆን ለዚህም በክልሉ በተፈጠረዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት ሁሉም ፕሮጀክቶች ወደ ስራ አለመግባታቸዉ እና የገቡትም ቢሆን ዘግይተ ወደ ስራ መግባታቸዉ እንዲሁም የተለያዩ የግንባታ ግብአቶችን በወቅቱ ማድረስ አለመቻል በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

በ9ወሩ የተመዘገበዉ አፈፃፀም ዝቅተኛ ቢሆንም ይህም በችግር ዉስጥ ሆኖ የተመዘገበ አፈፃፀም እንደሆነ በዉይይቱ የጋራ ግንዛቤ የተያዘ ሲሆን በቀጣይ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ጥረት መደረግ እንዳለበትም ተመልክቷል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top