የሀይቅ -ቢስቲማ-ጭፍራ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በመካሄድ ላይ ይገኛል

የሀይቅ -ቢስቲማ-ጭፍራ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በመካሄድ ላይ ይገኛል

************

የሀይቅ-ቢስቲማ-ጭፍራ 74 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የሀይቅ ቢስቲማ ጭፍራ የመንገድ ፕሮጀክትን ለመገንባት 2 ቢሊየን 233 ሚሊየን 149 ሺህ 775 ብር የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡ የፕሮጀክቱ የግንባታ አፈፃፀም 29.72 በመቶ ተከናውኗል።

የግንባታውን ሂደት ለማሻሻል በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በኩል የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ነው። የመንገድ ግንባታውን እያከናወኑ የሚገኙት ፓወርኮን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና አሰር ኮንስትራክሽን በጋራ በመሆን ነው።

የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን እየሰራ የሚገኘው ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ነው።

በመስመሩ ከዚህ በፊት ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ አውታር ያልተዘረጋበትና ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበረ ሲሆን ለአካባቢው ሕብረተሰብ ሆነ ለሀገራችን ያለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ይገኛል፡፡

መንገዱ በዋናነት የአፋርና የአማራ ክልሎችን በቅርበት በማገናኘት ማህበራዊ እድገት በማፋጠን ጥራት ያለዉ ፣ ምቹ እና ፈጣን የሆነ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ከማስቻሉ ባሻገር በአካባቢው በስፋት የሚገኙትን ማሽላ፣ ጫት እና የተለያዩ የፍራፍሬ ምርቶችን በማጓጓዝ የንግድ እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍ ያስችላል፡፡

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications

Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications

Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO

You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication

Website: https://www.amharacomm.gov.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *