ሰኔ 21/2015 ዓ.ም
በጎንደር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት በሳንጃ ማሰሮ የጥገና መስመር ላይ የተጀመረው የስላቭ ካልበርት ግንባታ ተጠናቀቀ=======
በጎንደር ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የክልሉ መንግስት በመደበው በጀት በ6 የጥገና መስመሮች የስላቭ ካልበርት ግንባታ፣ የድጋፍ ግንብ ግንባታና የስትራክቸር ጥገና ስራዎች እየተሰሩ ያሉ መሆኑ ይታወቃል።
ስለሆነም 39 ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው የሳንጃ ማሰሮ የጥገና መስመር ላይ የሚገኘው ድልድይ በ2014 ዓ/ም በክረምቱ ምክንያት በመፍረሱ አገልግሎት ተቋርጦ በተለዋጭ መንገድ ባልተመቸ ሁኔታ ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም በክረምት አገልግሎት መስጠት ስለማይችል የክልሉ መንግስት በበጀተው በጀት ብር 6,337,696 ባለ 6 ሜትር ስላቭ ካልበርት ድልድይ ግንባታው ተጠናቆ መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷል ።
መንገዱ ማስሮ ደንብን ከሳንጃ ከተማ የሚያገናኝ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትና ብቸኛ መንገድ በመሆኑ በድልድዩ መሰበር ምክንያት የተፈጥረው የአገልግሎት መቋረጥ በህብረተሰቡ ከፍተኛ መጉላላት ሲፈጥር ስለቆየ አሁን የድልድዩ መጠናቀቅ ይህን ችግር የሚፈታ በመሆኑ ህብረተሰቡ ክረምት ከበጋ የልተቆራረጠ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ ያደርገዋል።
.አቅዶ መፈጸም መገለጫ ባህላችን ነው !!
.ጥራት ያለው መንገድ ተደራሽ ማድረግ ተልዕኳችን !!
.የመንገድ ህይወቱ ጥገና ነው!!
ለተጨማሪ መረጃ
https://t.me/arrcao : Telegram Link
https://www.facebook.com/ARRCAGENCY : Facebook Link
https://twitter.com/ARRCA13 : Twitter Link
https://www.youtube.com/channel/UChvlxpLEzgiq4Ui2qcGrayg :YouTube Link





