የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ባለፉት 10 ወራት 3‚365.70 ኪ.ሜ የነባር መንገዶች ጥገና እና 33.74 ኪ.ሜ አዲስ መንገድ ግንባታ አከናወነ። የስትራክቸር ግንባታ ስራም እያከናወነ ይገኛል።
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በ2016 በጀት አመት በጎጃም፣ ደብረ ታቦር፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ወልድያና ሰሜን ሸዋ ጥገና ጽ/ቤቶች አማካኝነት 4‚560.63 ኪ.ሜ የነባር መንገዶች ጥገና ለማከናወን አቅዶ እስከ ሚያዚያ መጨረሻ 2016 ዓ.ም በነበሩት 10 ወራት በመደበኛና ወቅታዊ የጥገና አይነቶች 3‚365.70 ኪ.ሜ መንገድ በመጠገን የአመቱን እቅድ 73.80% አከናውኗል።
ባለፉት 10 ወራት በተከናወነው የነባር መንገዶች ጥገና ስራ በበጀት አመቱ ወደ ጥገና ከተገባባቸው 147 የጥገና መስመሮች መካከል 120ዎቹን ለማጠናቀቅ ተችሏል።
ኤጀንሲው በአዳዲስ መንገዶች ግንባታ ዘርፍም በበጀት አመቱ 93.89 ኪ.ሜ መንገድ ለመገንባት አቅዶ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት በሁሉም ፕሮጀክቶች ስራ መጀመር ባለመቻሉ አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ወደ ስራ በገቡ የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶች ብቻ የግንባታ ስራ እያከናወነ ይገኛል።
ኤጀንሲው በበጀት አመቱ ስራ በጀመረባቸው ፕሮጀክቶችም ቢሆን ዘግይቶ በታህሳስ ወር ወደ ስራ የገባ ቢሆንም እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ 33.74 ኪ.ሜ መንገድ በመገንባት የአመቱን እቅድ 35.93% ማከናወን ችሏል።
ከነባር መንገዶች ጥገናና አዳዲስ መንገዶች ግንባታ በተጨማሪ ኤጀንሲው የአነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ርዝመት ያላቸው ስትራክቸሮችን ግንባታ የሚያከናውን ሲሆን በበጀት አመቱ ወደ ስራ በገባባቸው 15 ፕሮጀክቶች አማካኝነት 67 አነስተኛ፣ መካከለኛና ትላልቅ ስትራክቸሮችን ግንባታ ለማከናወን ያቀደ ሲሆን በእነዚህ ፕሮጀክቶች አማካኝነት እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ 2016 ዓ.ም ድረስ በተከናወነው የግንባታ ስራ የተለያየ መጠን ያላቸው 10 ስትራክቸሮችን ግንባታ 100% ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን የ14 ስትራክቸሮችን ግንባታ አፈፃፀም ደግሞ ከ65- 97% ማድረስ ተችሏል። የቀሪዎቹ ስታራክቸሮች ግንባታ በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ይገኛል።
ኤጀንሲው በበጀት አመቱ ቀሪ ጊዜያት በአመቱ ለማከናወን ያቀደውን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል።





All reactions:
37Real Man When and 36 others