የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ሰራተኞች በኤች. አይ. ቪ/ኤድስ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄዱ።
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ሰራተኞች ከክልሉ ጤና ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች በያመቱ ህዳር 22 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የኤች. አይ. ቪ/ኤድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ዓለም አቀፋዊ ፣ አገራዊና ክልላዊ የኤች. አይ. ቪ/ኤድስ ነባራዊ ሁኔታን መሰረት ያደረገ ፅሁፍ ቀርቦ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ህዳር 27/2018 ዓ.ም አካሂደዋል።
የ2018 ዓ.ም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ38ኛ ጊዜ ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ37ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን የዘንድሮው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን በአገራችን "ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምላሽን እናረጋግጣለን!" በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።
ለኤጀንሲው ሰራተኞች በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዙሪያ ከተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ በተጨማሪ የአካል ጉዳተኞችንና ህፃናትን አስመልክቶ ከክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በውይይቱም አካል ጉዳተኞችና ህፃናት እንክብካቤና ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በመሆናቸው ሁሉም አካል ከማንኛውም ጉዳት ሊጠብቃቸው እንደሚገባ ግንዛቤ ተፈጥሯል ።



በ2017 ዓ.ም በተጠናቀቀዉ የባቲ-ጋሪሮ-ኤላ መንገድ ሥራ
ይናገራል ፎቶ፡-በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ወረዳ በ2015 ዓ.ም ተጀምሮ በ2017 ዓ.ም በተጠናቀቀዉ የባቲ-ጋሪሮ-ኤላ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት በ2017 ዓ.ም መጋቢት ወር ግንባታዉ ተጀምሮ በበጀት ዓመቱ የተጠናቀቀዉ እና 50 ሜትር ርዝመት ያለዉ የሀርቡ(አቧሬ) ወንዝ ድልድይ ገፅታ::

video and photo gallery
video and photo gallery
‹‹የአማራ ገጠር መንገዶች ድርጅት›› በሚል ስያሜ ጥቅምት 1987 ዓ.ም ራሱን ችሎ በአዋጅ ተቋቋመ፡፡
ይህን ስያሜ ይዞ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ለ20 ዓመታት የመንገድ/ድልድይ ግንባታ እና ጥገና እንዲሁም የኮንትራት አስተዳደር ስራዎችን ሲያከናውን ነበር፡፡ ኤጀንሲዉ በባለስልጣን ደረጃ የተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር7/1988 ዓ.ም በ1991፣በ1995 እና በ2005 ዓ.ም ወቅቱ የሚጠይቃቸዉ የአዋጅ ማሻሻያዎች ተካተዉበት አዋጁ እንደገና ተሻሽሎ በመፅደቅ ሲሰራበት የቆየ ሲሆን ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ከኮንትራት አስተዳደር ስራዎች ወጥቶ ‹‹የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ›› በሚል ስያሜ የመንገድ እና ድልድይ ግንባታና ጥገና ስራዎችን የሚያከናውን ተቋም ሆኖ በመደራጀት ተግባርና ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ኤጀንሲው በቀጣይ ከሚመለከታቸዉ አጋር አካላት ጋር ተባብሮ በመስራት የክልሉን ህብረተሰብ የመንገድ ተደራሽነት ጥያቄ ለመመለስ እና በክልሉ በመንገድ እና ድልድይ ግንባታና ጥገና ዘርፍ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ተቋም ለመሆን አልሞ እየሰራ ይገኛል፡፡