• Home
  • About Us
    • Organizational Profile
    • Vision and Mission
    • General Manager Message
  • Core Process
    • Road Construction
    • Road maintenance
    • Administration process
  • Anouncement
    • Vacancy
    • በኤጀንሲው የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ።
    • video and photo gallery
    • tender 2018
      • የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ 2018
  • Documentation
    • Directives and Proclamations
    • Standards and Manuals
  • External Links
    • Ministry Of Road
    • Road Bureau
  • 13.jpg
  • 15.jpg
  • 16.jpg
  • 17.jpg
  • 18.jpg
  • arrca1.jpg
  • arrca1fini.jpg
  • arrca2.jpg
  • arrca3.jpg
  • arrca4.jpg
  • arrca5.jpg
  • arrca6.jpg
  • arrca7.jpg
  • arrca8.jpg
  • arrca10.jpg
  • arrcamanager.jpg
  • atofen.jpg
  • atomeng.jpg
  • atomenke.jpg
  • chemet.jpg
  • chemet1.jpg
  • co17.jpg
  • COM1.jpg
  • com4.jpg
  • com5.jpg
  • com7.jpg
  • com8.jpg
  • com9.jpg
  • com10.jpg
  • com11.jpg
  • com12.jpg
  • com13.jpg
  • com14.jpg
  • com15.jpg
  • com18.jpg
  • com19.jpg
  • com91.jpg
  • com99.jpg
  • com178.jpg
  • com181.jpg
  • coms2.jpg
  • constleader.jpg
  • enag3.jpg
  • enag4.jpg
  • enag6.jpg
  • enag7.jpg
  • enag8.jpg
  • enag9.jpg
  • enagu9.jpg
  • ench.jpg
  • erp1.jpg
  • erp2.jpg
  • erp3.jpg
  • erp4.jpg
  • erpenagur.jpg
  • greendevelopment.jpg
  • hidase1.jpg
  • hidase2.jpg
  • hidase3.jpg
  • hidase4.jpg
  • hidase5.jpg
  • hidase6.jpg
  • hidase7.jpg
  • hidase8.jpg
  • plan2018-2.jpg
  • plan2018-3.jpg
  • plan2018.jpg
  • plan20181.jpg
  • pro1.jpg
  • pro2.jpg
  • pro3.jpg
  • pro4.jpg
  • pro5.jpg
  • pro6.jpg
  • pro7.jpg
  • pro9.jpg
  • pro10.jpg
  • pro11.jpg
  • pro12.jpg
  • roadmaintenance.jpg
  • sheme.jpg
Previous Next Play Pause
 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አመሰራረት

የ30ኛ ዓመት ምሥረታ በዓሉን ሰሞኑን ‹‹የተቀናጀ የቴክኖሎጂ ልማት ለመንገድ ጥራት እና ተደራሽነት!›› በሚል መሪ ቃል በድምቀት ያከበረዉ የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ከ1985-1986 ዓ.ም በክልሉ ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ስር ‹‹የገጠር መንገዶች መምሪያ›› በሚል በመምሪያ ደረጃ ከነበረበት አደረጃጀት ወጥቶ ‹‹የአማራ ገጠር መንገዶች ድርጅት›› በሚል ስያሜ ጥቅምት 1987 ዓ.ም ራሱን ችሎ በአዋጅ ተቋቋመ፡፡
  • enag3.jpg
  • enag4.jpg
  • enag6.jpg
  • enag7.jpg
  • enag8.jpg
  • enag9.jpg
  • enagu9.jpg
  • erp1.jpg
  • erp2.jpg
  • erp3.jpg
  • erp4.jpg
  • erpenagur.jpg
Previous Next Play Pause

መንገድ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ልማት ወሳኝ የመሰረተ ልማት ዘርፍ መሆኑን በመገንዘብ የህብረተሰቡን የመንገድ ተደራሽነት ፍላጐት ሊመልስ የሚችል ጠንካራ ተቋም ለማድረግ በማሰብ ከተቋቋመ ከአንድ ዓመት በኋላ ጥቅምት 3/1988 ዓ.ም ‹‹የአማራ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን›› በሚል ስያሜ እንደገና በአዋጅ ቁጥር7/1988 ዓ.ም ማሻሻያ ተደርጐለት በባለስልጣን ደረጃ ተቋቋመ፡፡
ይህን ስያሜ ይዞ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ለ20 ዓመታት የመንገድ/ድልድይ ግንባታ እና ጥገና እንዲሁም የኮንትራት አስተዳደር ስራዎችን ሲያከናውን ነበር፡፡ ኤጀንሲዉ በባለስልጣን ደረጃ የተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር7/1988 ዓ.ም በ1991፣በ1995 እና በ2005 ዓ.ም ወቅቱ የሚጠይቃቸዉ የአዋጅ ማሻሻያዎች ተካተዉበት አዋጁ እንደገና ተሻሽሎ በመፅደቅ ሲሰራበት የቆየ ሲሆን ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ከኮንትራት አስተዳደር ስራዎች ወጥቶ ‹‹የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ›› በሚል ስያሜ የመንገድ እና ድልድይ ግንባታና ጥገና ስራዎችን የሚያከናውን ተቋም ሆኖ በመደራጀት ተግባርና ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ኤጀንሲው በቀጣይ ከሚመለከታቸዉ አጋር አካላት ጋር ተባብሮ በመስራት የክልሉን ህብረተሰብ የመንገድ ተደራሽነት ጥያቄ ለመመለስ እና በክልሉ በመንገድ እና ድልድይ ግንባታና ጥገና ዘርፍ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ተቋም ለመሆን አልሞ እየሰራ ይገኛል፡፡

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ባለፉት 30 ዓመታት ከ6 ሽህ ኪ.ሜ በላይ የመንገዶች ግንባታ አከናወነ፡፡

 

የአማራ ገጠር መንገደች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋናው መ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች በኤጀንሲው የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ።

የኤጀንሲው የ2018 ዓ.ም የቁልፍ እና ዓበይት ተግባራት ዓላማዎችና ግቦች እንዲሁም ዝርዝር ተግባራትን ያካተተ የመንገድ ልማት ስራዎች እቅድ በ04/13/2017 ዓ.ም በኤጀንሲው የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል እና ግምገማ ደጋፊ የሥራ ሂደት መሪ አቶ ባሻ እንግዳው ቀርቦ በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች ውይይት ተደርጎበታል።


  


እቅዱ በቀረበበት ወቅት ኤጀንሲው በ2018 በጀት አመት ከክልሉ መንግስት በተመደበ ከብር 1.3 ቢሊዮን በላይ በጀት በ33 ነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶች 102.15 ኪ.ሜ መንገድና 227 ስትራክቸሮችን ለመገንባት እና ከፌዴራል መንገድ ፈንድ ጽ/ቤት በተመደበ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በ289 የጥገና መስመሮች 6‚038 ኪ.ሜ ነባር መንገዶችን ለመጠገን በእቅድ መያዙ ተገልጿል።

በውይይቱም የተቋሙ እቅድ ክልሉ ካቀደው የ25 አመት የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ፍኖተ ካርታ ከተወሰደ የ5 አመታት ስትራቴጅክ እቅድ መነሻ ተደርጎና የህዝብን የመልማት ጥያቄ ግምት ውስጥ አስገብቶ የተዘጋጀ በመሆኑ ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር ወጣ ባለ መልኩ መፈፀምን የሚጠይቅና የሁሉንም አካል የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ በተቋሙ ሰራተኞች ዘንድ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቀለሙ ሙሉነህ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት ኤጀንሲው የመንግስትና የህዝብን ተልዕኮ የተሸከመ ተቋም በመሆኑ ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል የሚለውን በአግባቡ ይዞ መስራት የሚጠበቅ ሲሆን እቅድን፣ ሀብትንና የሰው ሃይልን በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት ከአመራሩ እንደሚጠበቅና ሰራተኛውም የእቅዱ ባለቤት መሆን፣ የታቀደውን እቅድ ለመፈፀም ቁርጠኛና ተነሳሽ መሆንና ስራን በጋራ፣ በቅልጥፍናና በቅንነት በመስራት እቅዱን ማሳካት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

 

Page 3 of 4

  • Start
  • Prev
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • Next
  • End
 

Recently Updated Posts

  • የአማራ ገጠር መንገደች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋናው መ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች በኤጀንሲው የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ።
  • ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 1- 2018
  • የሀዘን መግለጫ
  • 2017 nine month
  • Message From General Manager

  • facebook
  • google+
  • twitter
  • instagram
  • Youtube
  • Whatsapp
 

All Rights Reserved © 2025 Amhara Rural Road Construction Agency