የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ12 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለበዓል መዋያ የሚሆኑ የተለያዩ ድጋፎችን አበርክቷል።
በኤጀንሲው ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በባህር ዳር ከተማ በዓታ ቀበሌ አስተዳደር አማካኝነት ተለይተው የተላኩ 10 ግለሰቦችና 2 የተቋሙ ሰራተኞች በድምሩ 12 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሲሆኑ ለእያንዳንዳቸው 5 ሊትር ዘይት፣ 5 ኪሎ ሽንኩርት፣ 1 ዶሮ፣ 12 እንቁላል እና ከ10 እስከ 25 ኪ.ግራም የፊኖ ዱቄት በአጠቃላይ 51‚000.00 (አምሳ አንድ ሺህ ብር) የሚገመት ድጋፍ ተደርጓል። ድጋፍ ከተደረገላቸው ግለሰቦች መካከል 11ዱ ሴቶች ናቸው።