የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አመራሮች እና ሰራተኞች በየዓመቱ የሚከበረዉን የፀረ- ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዉይይት አካሄዱ፡፡
የኤጀንሲዉ ዋና መ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች ‹‹ትዉልድን በሥነ-ምግባር፤ተቋምን በአሠራር›› በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የፀረ- ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዉይይት በ29/03/2018 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡
በዉይይቱ የተቋምን አሠራር ማዘመን ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል ትልቅ ፋይዳ ያለዉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ለዚህም በተቋማት የዲጂታል ቴክኖሎጂ አሠራርን የማጠናከር ተግባር በትኩረት መሰራት ያለበት መሆኑ ተመልክቷል፡፡
አሠራርን ከማዘመን ባሻገር አመራሩ እና ሰራተኛዉ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን ተላብሶ ተግባራትን ማከናወን ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የማይተካ ሚና ያለዉ በመሆኑ የአመራሩ እና ሰራተኛዉን ሙያዊ ሥነ-ምግባር ለማጎልበት የሚያስችሉ ተከታታይ ተግባራት መከናወን እንዳለባቸዉም በዉይይቱ ተገልፆል፡፡




የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ (ድጋሚ የወጣ ግልፅ ማስታወቂያ)፣
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በ2018 በጀት አመት ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች የሚያገለግሉ፡-
• የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ (ድጋሚ የወጣ ግልፅ ማስታወቂያ)፣
• ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር እና የድልድይ ቤሪንግ፣
• ሲሚንቶ ከነትራንስፖርቱ እንዲሁም
• ለተቋሙ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የእስቴሽነሪ፣ አላቂ የፅዳት እቃ፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የህንፃ መሳሪያዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ግልፅ ጨረታ አውጥቷል።
ዝርዝሩንም ከጨረታ ማስታወቂያው መመልከት ይቻላል።


